Fight the Good Fight of Faith, Amharic Edition
ትምህርት 7 እኛ የምንዋጋው ጠላት • 93
ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል። ስለእዚህ እውነት ያለን ትክክለኛ ግንዛቤና መረዳት በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ፈተናን ለመቋቋም እንድንችል የሚረዳን እንዴት ነው?
ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል አድራጊነትን ለሚሰጠን ለአምላካችን ልባዊ ምስጋናችንን ሁልጊዜ እናቅርብለት (1 ቆሮ 15፡57)! ከዲያቢሎስ ሃይል ነጻ ወጥተናል፣ ከጨለማው መንግስት ነጻ ወጥተናል፣ በመስቀል ላይ በፈሰሰው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነፃ ወጥተናል፣ እንደ አዲስ ሃገር ዜጋ ተቀብሎናል፣ በተሰጠንም አዲስ ስልጣን እና በእግዚአብሔርን ተወዳጅ ልጅ መንግስት እንመካለን(ቆላ. 1:13 )። ይህ ታላቅ ድል የእኛ ነው፤ ነገር ግን ጠላታችንን መቋቋም፣ መልካሙን የእምነት ገድል መጋደልን መቀላቀልን እና በዚህ ውጊያ ውስጥ እንደ ተዋጊዎች ትግል ማድረግን መማር ያስፈልገናል። ክሪስተስ ቪክቶርን (ለኢየሱስ የተሰጠ ማዕረግ ሲሆን “ክርስቶስ ድል ነው” ማለት ነው) ለመወከል የተጠራችሁባቸውን ቦታዎች አስቡ- በቤተሰባችሁ ውስጥ፣ በጓደኞቻችሁ መካከል፣ በጎረቤትቻችህ ዘንድ፣ በስራችሁ እና በስራችሁ አጋጣሚ የሚያገኙዋቸው ሰዎች ጭምርም ነው። እናንተ አሁን የክርስቶስ ወታደር ናችሁ (2ኛ ጢሞ 2፡1-8) እናም በጠላቶቻችሁ ላይ የማያቋርጥ ጥቃቶችን በመፈጸም ፊትለፊት ጸንታችሁ ለመቆም ተጠርታችኋል። በዚህ ውጊያ ውስጥ ልንማር ከሚገባቸው የመጀመሪያ ነገሮች ውስጥ አንዱ የራሳችንን ንግግር ከእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ጋር እንዴት ማገናኘት ወይም አንድ ማድረግ እንዳለብን ነው። እኛን የሚያጋጥመን ሁኔታዎች ሳይሆኑ እኛን የሚጎዱት ይልቁነም እኛ ለራሳቸን የምንናገራቸው ሃሳቦች ናቸው የሚሰማንን ስሜት እና የምናደርጋቸውን ድርጊቶች ተጸዕኖና ጫናን የሚፈጥሩብን። በመሆኑም ስለዚህ ታላቅ ጦርነት፣ ስለ ማንነታችን፣ ስለ ክርስቶስ ድል እና ጌታ ድል እንድናገኝ የሚረዳን ሃብትን በተመለከተ እውነታውን ለራሳችን ስለመንገር መማር አለብን። ስለ ራሳችን የምንናግረው ሃሳቦች (እኛ የምናምንባቸው ነገሮች) ምን እንደምናደርግ የሚወስኑ ስለሆነ፤ እኛ ለራሳችን የመናገር ምርጥ የሆኑ አዲስ ልማዶችን መማር አለብን። ኢየሱስ በክፉው ኃይል ላይ እንዳሸነፈ በማረጋገጥ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመስማማት እናም ለእግዚአብሔር ስንገዛ እና የዲያብሎስን ውሸቶች ስንቃወም ዲያቢሎስ እንደሚሸሽ መማር አለብን። መንፈስ ቅዱስ ስታምንባቸው ስለነበሩ ሃሰቶች ግንዛቤን እንዲሰጥህና እንዲጠቁምህ መጠየቅን አሁን (ዛሬ)ጀምር። ህይወትህን በእግዚአብሔር ቃል እውነት እና በክርስቶስ ባለው ድል ለመተርጎም ይቃኙ እንጂ፤ ነገሮች ምን እንደሚመስሉ ወይም እንዴት እንደሚሰማዎት በማሰብ ላይ አይደለም። አዲስ የአስተሳሰብ ልምድ መማር ጊዜ ይወስዳል ስለዚህ ታገሱ። የክረስቶሰን እውነት ባረጋገጡና ባጸኑ መጠን እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶሰ ያገኙትን ድል ባወጁ መጠን የጠነከረ ኃይልን ታገኛላችሁ በመንፈሳዊ ውጊያዎች የበለጠ ውጤታማ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል። አዳዲስ የአመለካከት ስርዓቶችን፣ አዲስ ልምዶችን እና አዲስ የአስተሳሰብ ንድፎችን ሲፈጥሩ እግዚአብሔር ጥንካሬን እንዲሰጥዎት ዛሬ ይጠይቁ። ይህን በምትሰሩበት ጊዜ ኢየሱስ ለእናንተ ባቅዳጀው የድል ህይወት ውስጥ ትኖራላችሁ፣ ተስፋ መቁረጥ እና የስሜት ቀውስ ትከላከላላችሁ እንዲሁም በክርስትና ሕይወትዎ ውስጥ ወደ ብስለት ያድጋሉ።
ማዛመድ
ከመንግሥቱ ሥራ ሊያስተጓጉለኝ የሚሞከረ ጠላት አለኝ፣ ስለሆነም አዳዲስ መከራዎች ሲመጡብኝ አዲስ ነገር እንደመጣብኝ አለደነቅም።
ማጽናት
የካንተርበሪው አንስለም (1033 - 1109) በፈረንሳይ የተወለደ እና በኋላም የእንግሊዝ የቤተክርስቲያን መሪ ሆነ። በስነ-መለኮት ላይ በፈጠረው ተጽእኖው ምክንያት “የልሂቃን መስራች” ተብሎ
ጸሎት
Made with FlippingBook - Online magazine maker